top of page

ወንጌል ለኢትዮጵያውኖች ማለት ለምን አስፈለገ?

ይህ ድኅረ ገጽ ከዚህ ቀደም ከአንድም ሁለት ስሞች ነበሩት። ሲጀመር የሁለተኛው መጽሐፌ በታተመበት ጊዜ፣ መጽሐፉን ለማስተዋወቅ የጀመርኩት ድኅረ ገጽ ነበርና "የተሻለ እውነት በደብዳቤ" የሚል ስያሜ ሰጥቸው ነው የጀመርኩት።

ከጊዜ በኋላ ተጨማሪ ጥናቶችን እያካሄድኩኝ ስመጣ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለመድረስ ከመፈለግ የተነሳ "ወንጌል ለኦርቶዶክሳውያን" በሚል ርዕስ "gospel4ethiopianorthodox" የሚል ስያሜ ሰጠሁት። በዚህ ስም አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያን ተከፍተው እንደነበር የገለጹልኝ አሉ። እንዴት ለእኛ ወንጌል ይሰበካል። እኛ አጥብቀን እናውቀው የለ እንዴ? ወይ ስሙን ቀይር ወይ ገጹን ከነአካቴው አውርደው ያሉኝም አሉ። እኔም ሽንጤን ገትሬ የለም በመጽሐፍ ቅዱስ ከሚገኘው ወንጌል ጨምራችሁ በመጀመሪያቱ ቤተ ክርስቲያን ያልነበሩ የእምነት አቋሞችና ሥርዓቶች በመጨመራችሁ ወደ መሠረቱ መመለስ ያስፈልጋችኋልና አልቀይርም፣ አላነሳም አልኩኝ።
ይኸው አቋሜ እንደተጠበቀ ሆኖ - ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ በፕሮቴስታንቱ የእምነት ከፍል እየተሰፋፋ የመጣው የስህተት ትምህርት በጣም አሳሳቢ አልፎም አስጨናቂ እየሆነ በመጣበት ጊዜ ወንጌል ለፕሮቴስታንቱም የእምነት ክፍል እንደ ገና መሰበክ፣ እንደ ገና ተቆፍሮ መሠረት መተከል አስፈላጊ ሆኗል። ስለዚህ የድኅረ ገጹን ስም ለሦስተኛ ጊዜ ተቀይሮ "ወንጌል ለኢትዮጵያውያን" ተጽሎ ተሰይሟል። 

አዲስ ስም እንደመውጣቱ በድኅረ ገጹ በአዲስ መንፈስ የተሻለ እንቅስቃሴም ለማድረግ አቅጃለሁና እግዚአብሔር በረዳን መጠን ብቅ ብቅ እላለሁ።

አመሰግናለሁኝ!!

The name for this website is being changed for the third time. it used to be 'yeteshaleewenet.com' under the title of my second book 'Yeteshale Ewenet Bedebdabe'. Then, as I continued my research into the Ethiopian Orthodox Church and started studying the teachings of different EOC church leaders and teachers, the realization that the majority of the EOC teachings and doctrine are not aligned with and at times are contradictory to the Gospel that was taught by Jesus Christ, preached by the martyred Apostles and followed by the Early Church, became very apparent. And I changed it to "Gospel4Ethiopian Orthodox". This change of name created some heated discussion with members of the Orthodox Church. They argued how dare I wanted to preach the gospel to them as if they did not know and believed in it? 'Either change the name or take the website down' was their ultimatum!

 

While the above position has not changed for me, however, recent growth of false teachings among Protestant churches in our communities has become alarming and concerning. It made realize that the preaching of the foundational Gospel of Jesus Christ to the Protestant congregations has become an urgent necessity. And so I am being compelled to change the website's name, for the third time, to "Gospel4Ethiopians".

With this new title, I am also hoping that I will increased capacity and activity to share educational and engaging materials on the website, with the Grace of God.

Thank you

እንኳን በደህና መጣችሁ
Welcome
Bienvenue

LG Photo for 2021.jpg
Subscribe to Our Mailing List
በየወቅቱ መረጃዎችን ማግኘት ከፈለጉ እዚህ ይመዝገቡ
bottom of page